Yahodee Masqala in Hadiya Ethiopia

ያሆዴ የሃዲያ ህዝብ ታላቅ ባህላዊ የአዲስ አመት ክብረ በአል ነው እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም

Click here to read the English version of this article.

ወር ሙሉ የሚከበረዉ ያሆዴ አንዷን ቀን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመስቀል ቀን ጋር መጋራቱ የመገጣጠም ጉዳይ ነው።

የያሆዴን በዓል ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት በሆነው የክርስቶስ መስቀል ግኝት ጋር የማያያዙ ዝንባሌ ኢትዮጲያ ውስጥ በስፋት ይስተዋላል፡፡ ይህ በሀዲያ እና በሌሎች የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ በታላቅ ደስታ የሚከበረውና ወር የሚዘልቀውን የአዲስ ዘመን መግቢያ ሥነ-ስርዓት ከእየሱስ ክርስቶስ መስቀል ግኝት ጋር ማያያዝ ፈፅሞ የተሳሳተ አረዳድ ነው፡፡

ይህ ማለት ግን ይሄን አፈ-ታሪክ የፈጠረችው ቤተ ክርስቲያን ናት ማለት አይደለም፡፡ በሀገር ደረጃ በሀዲያ እና ሌሎች የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ታሪክ ፣ ባህል ፣ እና ዕሴቶች ዕውቀት ማነስ ጋር ተያይዞ እየደረሱ ያሉትን የታሪክ መጣረሶችን መለየት አለብን፡፡ ባህላቸውም ሆነ ታሪኮቻቸው እየተገለለ መምጣቱም ቢሆን ብዙም የማያስደንቅ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡

በዚህ መልኩ መተርጎሙ ለቤ/ክ አግባብነት ያለው ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን በዓሉ ለሀዲያ ሕዝብ ካለው ትርጉም አንፃር በዚያ መልኩ ማዋሃዱ ተገቢ ያልሆነ ነው፡፡ ይህ ማለት ታሪክን እንደገና መፃፍ እንደማለት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ለሕዝቡ ሌላ የሌለ ታሪክ ከመፍጠር ጋር ሁሉ ሊስተካከል ይችላል፡፡

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፣ በፕሮቴስታንቱም ሆነ በካቶሊክ እምነት ተከታይ የሀዲያ ሕዝብ ዘንድ እነዚህን ሁለቱን በዓላት በጣምራ ማክበሩ ቅሬታ ፈጥሮበት አያውቅም ምክንያቱም ሁለቱም በዓላት በታሪክም ሆነ በባህል የተለያዩ ዕሴቶች መሆናቸውንና የቀናቱም መገጣጠም የአጋጣሚ ነገር መሆኑን በሚገባ ተገንዝቦታልና፡፡

በኢትዮጲያ በበላይነት ተንሰራፎ የሚገኘው ባህል የያሆዴ ባህላዊ ፋይዳውን በመተው በዓሉን በሀይማኖታዊ በዓልነት በመፈረጅ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች ጥንታዊ ቅርሶቻቸውንና ባህላቻውን እንዳያስጠብቁ አድርጓል፡፡ በመስቀል በዓል ዕለትም ኢቲቪ ፣ ዋልታ ፣ ፋና እና ሌሎች ማሰራጫዎችም ስርጭታቸውን ‹‹ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ›› በማለት ነበር የከፈቱት፡፡ ከህዝቡ በሚሰበሰበው ታክስ በሚተዳደሩ ሚዲያዎች ላይ እንዲህ አይነቱ ስርጭት መተላለፉ የሀዲያን ማህበረሰብ እጅግ ያስቆጣል፡፡

ለዘመናት በተደጋጋሚ ሲሰራጩ በነበሩ በእነዚህ እና በሌሎች የታሪክ መበረዞች ምክንያት አንዳንድ የሀዲያ ሙስሊም ማህበረሰብ ራሳቸውን ከዚህ ታላቅ ዘመን መለወጫ በዓል ሲያገሉ ተስተውለዋል፡፡ ይህ መገለል በሀገር ደረጃም እየተስተዋለ መሆኑን ተገንዝቤያለው፡፡

ያደግኩት በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ቤተሰብ ነው፡፡ እኔ የሁለት አመት ሕፃን በነበርኩበት ወቅት ነበር ቤተሰቦቼ ከእስልምና ወደ ፕሮቴስታንት እምነት የተቀየሩት፡፡ አብዛኛዎቹ የዘር ሀረጎቼ እስካሁንም ድረስ የእስልምና እምነትን በመከተል ላይ ናቸው፡፡ ከሁለቱም ቤተ እምነት ተከታዮች ጋር የቅርብ ግኑኝነት ስለነበረኝ በሁለቱም የሀይማኖት ጎራዎች ስላሉ ልምምዶች እንግዳ አይደለሁም፡፡

ያሆዴ ለክርስቲያኑ ቤተሰቦቼ የተቀደሰ በዓል እንደመሆኑ ሁሉ ለሙስሊሙ ቤተሰቦቼም እንደዛው ነበር፡፡ ሊመሰገን በሚገባ መልኩ እስካሁን ድረስ በሁለቱም ቤተሰቦቼ ዘንድ በተለየ ድምቀት ይከበራል፡፡ ከክርስትና እምነት ጋር ብቻ መያያዙ በሌሎች የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለበዓሉ ያለው ክብር ሊሻር ይችላል የምል ስጋት አለኝ፡፡

የተሳሳተ ትርጓሜ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤቶቸ

  • ከለምንም ታሪካዊ መሰረት ያሆዴን ሃይማኖታዊ በማድረግ የሀዲያ፣ የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ብሎም የመላው ኢትዮጲያ ሙስሊሞችን ከበዓሉ ያገላል፡፡ ይህ ተግባር አያቶቻቸውና ቅድመ አያቶቻቸው ለዘመናት ካከበሩትና ከተደሰቱበት በዓል ሙስሊሞ ልጆቻቸዉን ማግለል እንደማለት ነው፡፡
  • ለመጪው ትውልድ የተዛባን ታሪክ ማውረስሞ ይሆንብናል ፡፡
  • የህዝብን ባህል ፣ ልማድ እንዲሁም የኑሮ ዘይቤን ማንኳሰስ ይሆንብናል፡፡ ያሆዴ ለሀዲያ ከማንነቱ ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው፡፡
  • ጎልቶ የሰፋነዉ ባህል የተጎዳ ባህል ያላቸዉ ብሄሮችን የባህል እሴቶች እንደመናድ ነዉ

የ‹‹ያሆዴ›› እና ‹‹መስቀል›› ልዩነት ማስረጃዎች

What are the evidence that Yahoode Masqala, most sacred of annual celebrations, is not the same as Mesqel observed by Christians around the same time of the year? Here are a few:

  • ኦርቶዶክስ ሀይማኖት በሀዲያ እና በአብዛኞቹ የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ውስጥ ታሪክ ያለዉ እንኳን ቢሆን የአብላጫነት ያለዉ ሀይማኖት ሆኖ አያውቅም፡፡ ማህበረሰቡ ዘንድ አንድም ቀን የአብላጫ ሀይማኖት ሆኖ ከማያውቀው ሀይማኖት በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ክብር ያለው ያሆዴ በዓል ሊወለድ አይችልም
  • ያሆዴ ማንኛቸዉም የክርስትና ተፅዕኖዎች ወደ ሀዲያ ከመምጣታቸዉ በፊት የኖረ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ክርስትና ታሪክ በመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ከያሆዴ ጋር ሲነፃፀር ውስን ነው፡፡ የፕሮቴስታንት እምነት ደግሞ እጅግ በጣም ውስን ነው፡፡
  • ያሆዴ ለሀዲያ እና ለሌሎች የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች የአዲስ ዓመት መግቢያ (መጀመሪያ) ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይህ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አብላጫ በሆኑባቸዉ አከባቢዎች እንኳን አይታሰብም፡፡
  • በሀዲያ ማህበረሰቡ ዘንድ ከበዓሎች ሁሉ የበላይና ትልቅ ክብር ያለው ያሆዴ ሲሆን ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ግን የኢየሱስ ትንሳኤ (ፋሲካ) ነው። ያሆዴ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት መሰረት ቢኖረዉ ይህ ሊሆን አይችልም
  • ያሆዴ በእስልምናም ሆነ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላለፉት ብዙ ትውልዶች በአንድነት ማክበራቸው ይህ በዓል በሀዲያም ሆነ በሌሎች የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ዘንድ ከየትኛውም ሀይማኖት ጋር ግኑኝት የሌለው መሆኑን የመላክታል። ከክርስትና ጋር ማጣመር የዛሬ ክስተት ነዉ

በእነዚህ ምክንያቶች ጋዜጠኞች ድንቁርናን ከማሰራጨት ይልቅ ሰዎችን ለማስተማር እና ለመማር ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡ አንትሮፖሎጂስቶች፣ የታሪክ ምሁራን እና ሌሎች ተመራማሪዎች ይህንን ጨምሮ በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ አፈ፡ታሪኮችን ማረም መጀመር አለባቸው፡፡ በጌጥ ካሸበረቁ ቢሮዎች ወጥተው በታዋቂ የብዙኃን መገናኛዎች የእነዚህ በዓላትን እውነተኛ አመጣጥ ለህዝቡ ማስተማር ይገባቸዋል፡፡ የሀዲያ ህዝብ እና ሌሎች የመዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እነዚህን እየተዛቡ ያሉትን የታሪክ ዕሴቶቻቸውን ለመጠበቅ መታገል መጀመር አለባቸው፡፡ ይህን የማድረግ ልዩ ግዴታ አለባቸው፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

4 thoughts on “ያሆዴ የሃዲያ ህዝብ ታላቅ ባህላዊ የአዲስ አመት ክብረ በአል ነው እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም”