ሰለ ደቡባዊ የኢትዮዽያ ቀጠናም ሆነ ሰለ ሀድያ ዞን ሰሞኑን በሚዲያዎች በስፋት የሚሰራጩትን ዘገባዎች ስንከታተል ቆይተናል። በቅድሚያ በሲዳማ ዉስጥ ስለጠፋዉ ህይወትና ሰለተጎዱ ዎገኖቻችን ጥልቅ ሀዘናችንን እንገልፃለን። በኛ እምነት ይህን ክስተት በቅድሚያ መከላከል ይቻል ነበር። የተከሰቱትን ነገሮች በዚህ ጽሁፋ አንዘረዝርም። ትኩረረታችንን በሀዲያ ዞን በኋላ ስለተፈጸሙ ነገሮችና ተያያዥ ጉዳዮች ለይ ለማድረግ እንሞክራለን። ከዘገባዎቹና ባደረግነዉ ክትትል የሚከተሉትን ነገሮች ለመረዳት ችለናል ፦
- ደኢህዴን አወዛጋቢ፣ ግልጽነት የጎደለዉንና፣ ኢ-ህገ መንግስታዊ መግለጫ ማዉጣቱን፣
- ደኢህዴን ሰላማዊዉን የሀዲያ ቀጠና በኮማንድ ፖስት ሥር እንዲወድቅ ማድረጉን ፣
- ደኢህዴን ፍጹም አምባገነናዊ በሆነ መልኩ የሀዲያንና የሲዳማን ከፍተኛ አመራሮች ከስራ ማገዱን፣
- ፖለትከኞች ለራሳቸዉ ግብ መጠቀሚያ ያደረጉት የኢትዮዽያ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም በዋቸሞ (ሆሳዕና) ከተማና ዙሪያው በሞተር ብስክሌት እየተንቀሳቀሱ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደርን ሥራቸዉ ያደረጉ ሰላማዊ ወጣቶችን እያስቆሙ ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ወከባ እያደረሱባቸዉ ነዉ የሚል ዘገባ ሰምተናል፣
- ሀዲያ የኢትዮጵያ ህገመንግስት ያጎናጸፈውን መብት በመጠቀም የጠየቀውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ በአግባብ አለመመለሱን ተከትሎ ለሀዲያ መብት የሚታገሉት ወጣቶች (ከቤራዎች) ለሀምሌ 17/2011 አቅደዉ የነበረዉን ፍጹም ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በክልል ደረጃ በታወጀው ኮማንድ ፖስት ምክንያት ለማራዛም ተገድደዋል፣
- የሀዲያ በክልልነት መደራጀት የእግር እሳት የሆነባቸው አካላት፤ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ የከቤራ ትግልንና የሃምሌ 17ቱን ሰላማዊ ሰልፍ በማጠልሸት ወሬዎችን ነዝተዋል፣
- እነዚሁ አካላት ከሀዲያ ጋር ለዘመናት አብሮ የኖሩትን (በቀጣይም የሚኖሩትን) የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የከምባታና ሌሎች ኢትዮዽያዊ ወገኖቻችን ስጋት ዉስጥ ለማስገባት የናንተን የንግድ ማዕከላትንና ቤቶችን ለማወክ፣ ለመዝረፍና ለማቃጠል የታቀደ ነው እያሉ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ አሰራጭተዋል፣
- እነዚህንም መጥፎ ተግባራት አስተባባሪው አያሌው ዝና (ተወጋጅ የዞን አስተዳዳሪ) እንደሆነ አድረገው አስወርተዋል፣
- በሙስና፣ ብልሹ አሰራር፣ በመሬት ወራራና በሌሎች ሕገ ወጥ መንገዶች የበለፀጉ ግለሰቦችና ባለሃብቶች ማንኛዉም ለሀዲያ መሰረታዊ መብቶቹን የሚመልስለት ለዉጥ ጥቅማቸዉን የሚነካ ስለሚመስላቸዉ የዚህ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ አካል ሆነዋል
እነዚህንና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን በማገናዘብ በሰሜን አሜሪካ የሚንኖር የሀድያ ተወላጆች የሚከተሉትን ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
- ሀዲያ ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ የአስተዳደራዊ ታሪካዊ ምዕራፎችን ያየ ህዝብ ነዉ። በጥንታዊዉ ዓለም ራሱን የቻለ ሀገር አድርጎ ራሱን የገዛበት ዘመናት፣ በኮንፌዴሬሽን ከመሠል እስላማዊ ሱልጣኔቶች ጋር አጋር ሆኖ ራሱን የገዛበት ዘመናት፣ እና ሰሜናዊ መንግስታት አገዛዝ ሥር ወድቆ ራስ ገዝነትንና እኩልነትን ያጣበት ዘመናትን መጥቀስ ግድ ነዉ። ራስ ገዝነትን ባጣባቸዉ ዘመናትም ቢሆን ለእኩልነትና ራስን በራስ ለመግዛት ከመታገል የተቆጠበበት ዘመን አይገኝም። ለዚህም ማሳያ የሚሆን ወደ ሩቅ ቀደምት ታሪክ ዉስጥ ሳንገባ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ምርጫዎች ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግን በምርጫ የሸነፈና ለዚህም አያሌ ልጆቹን ለሞት፣ ላካል ጉዳት፣ ለእስር፣ ለእንግልትና ለስደት የገበረ ኩሩ ሕዝብ ነው። በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ በዞኑ ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ክልል ምክር ቤት በታህሳስ ወር 2011 ዓ.ም ከተላከበት ጊዜ ጀምሮ ምላሽ እየተጠባበቀ ይገኛል። ይህ ጥያቄ በሕገመንግስቱ አግባብ እስከ አንድ አመት ጊዜ የማይመለስ ከሆነ ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት የሀዲያ ሕዝብ በክልል የመደራጀት መብቱን በመጠቀም የራሱን ክልል ለማወጅ የሚገደድ መሆኑ አውቆ፣ የሚመለከተው አካል ያለምንም ማዛግየት ምላሽ እንድሰጥ እንጠይቃለን፣
- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሰላማዊ ህዝብ ላይ የተወጀዉ ደኢህዴን በሁሉም የደቡብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ድርጅቱ ፍጹም የተተፋ ከመሆኑም በላይ ተቀባይ አጥቶ የሞት አፋፍ በተጠጋበት ወቅት ስለነበረ ሕልውናዉን ለማዳን አጋጣሚዉን ስላገኘ እንደሆነ እናምናለን። የታወጀዉ የሲዳማ ዞን እንኳን ከተረጋጋ በኳላ ሆን ተብሎ ስላማዊዉን ህዝብ ለማሸበር የተደረገ መሆኑን ልናስታዉሳችሁ እንሻለን። የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ይህን በመፈንቅለ መንግሥት በተሞከረበት ክልል እንኳን ያልታሰበዉን የሽብር አዋጅ በኣስቸኳይ እንዲያነሳ በጥብቅ እንጠይቃለን
- አሁኑኑ ደግሞ በሀዲያና በዞኑ ባሉ ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተገን በማድረግ በህዝቡ ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችን (ሰብዓዊና ዴክራሲያዊ መብቶች) ማለትም ማዋከብን፣ ማሰርን፣ አስገድዶ መድፈርን፣ ንብረት መቀማትን፣ ማሸማቀቅን ወዘተ) መንግስት በአስቸኳይ እንዲያቆም እናሳስባለን፦
- የከቤራ ትግል ከሀዲዮማ/ከሀዲያ ማንነት/ ጎን ለጎን የሀዲያንና አብሮ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የጋራ ተጠቃሚነት እንድረጋገጥ ያለመ በመሆኑ በቀጣይ በአንድነት እየሰራን የተጀመረው ትግል የሚንቀጥል ሲሆን፤ ስለ ሀዲያ እና አብሮ ስለሚኖሩት ማህበረሰቦች የሚወስነው ይሄው የማህበረሰብ ክፍል እንጅ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳና በሌሉችም ትልቅ ከተሞች ሆነዉ ህዝባዊ ወገንተኝነት የሌላቸው ቡድኖች እንዳልሆነ እንዲታወቅና ከነሱ ጋር በየትኛውም መልኩ የሚተባበር ሁሉ ለሀዲያ ሕልውና በተቃራኒነት እንደቆመ የምንቆጥር መሆኑን እንዲታወቅ እንፈልጋለን፣
- ከላይ የተጠቀሱትን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጩ አካላት ከሴራቸዉ እንዲታቀቡ በጥብቅ እናስጠነቅቃለን፣
- በሌላ መልክ የተከሰተዉ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ደግሞ ከቤራ ለሐምሌ 17 ታቅዶ ለነበረዉ ሰላማዊ ሰልፍ እርዳታ መጠየቂየ ማስፈራሪያ ያዘለ ደብዳቤ ጽፎ ነበር የተባለዉ ነዉ። ከቤራ በፍፁም እየተወራ ያለውን ዛቻም ሆነ የማስፈራሪያ ደብደቤ እንዳልጻፈ የደረስንበት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
በሰሜን አሜሪካ የምንኖር የሀዲያ ብሄር ተወላጆች
1-Aug-2019
One thought on “ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ ከሀዲያ ተወላጆች የተሰጠ የአቋም መግለጫ”
hadiya ba manges derejam yetanakach nati beyenw masebw seltan yeyaze hulu bagnalaynew ende seltanuni measayew ye abiy mangist aynu yebada esu seltanuni ba hadiyawoch leasaynew wotadarochun yelakaw ? ba aschokay mawtat alebachw kangide selamawe salf sayhon yetakawimo salf new mahon yalebat ka Minilik zeman anseto iskahunderes menakachen aybekam ende leloch kililoch zonoch woredawoch kabalewoch saykare lewt senorachw la hadiyoch men lewt alachew ye hadeyawoch lawt sidat bicha new be sidet iyaleku menornew mengist menabatu la hadiya mangist ayasfaligim ye abiy mangist funifun malet bich enje menim aytakim nonsens