ይህም የመንግስትን የራሱን የ2007( እ.አ.አ.) የህዝብ ቆጠራ ብቻ በመጠቀም ነዉ።
ይህ chart ለማሳየት የሚሞክረዉ በኢትዮዽያ ትልልቆቹን ብሄሮች የህዝብ ቁጥር በ% ስዕል ነዉ። ሰብዓዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ራስን በራስ ማስተዳደር መብት የሚወሰነዉ በማንኛዉም ሀገር በህዝብ ብዛት መሆን የለበትም። ቻርቱ እንደሚየሳየዉ የሀዲያ የህዝብ ብዛት ቶፕ ቴን (top ten) ዉስጥ ከመሆንም አልፎ በ 8ኛነት ይታያል። ሆኖም የሀገሪቷ ፖሊሲ ሲታይ ለደቡብ ኢትዮዽያ ብሄሮች መብታቸዉ የሚገደበዉ በህዝባቸዉ ቁጥር ሳይሆን ደቡብ ዉስጥ በመሆናቸዉ ብቻ መሆኑን ነዉ።
ቢቢስ (BBC) 8 ትላልቅ የኢትዮዽያ ብሄሮች ናቸዉ ብሎ ካቀረባቸዉ ዉስጥ 4ቱ የሚገኙት በደቡብ ኢትዮዽያ ሲሆን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በክልል ለመደራጀት ሕገ መንግስታዊ መብታቸዉን ጠይቀዉ ያገኙት ምላሽ በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ እዉነት እኛ እንደ ሙሉ ዜጋ እንታያለን ወይ ብሎ ራሱን እንዲጠይቅ አድርጎታል። ከ8ቱ ዉስጥ የሌሉ ግን ደቡብ ዉስጥ ያልሆኑ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉምዝና ሀረር የክልልነት መብታቸዉ በተገቢ መልኩ ተጠብቆላቸዋል፣
መብታቸዉ ካልተከበረላቸዉ 4ቱ ዉስጥ ስዳማ ጠንከር ያለ እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረጉ ከብዙ ማንገራገርና ማዘግየት በኋላ ጥያቄዉ ህዝበ ዉሳኔ ቀን ተወስኖለታል። ይህ ማንገራገርና ማዘግየት አላስፈላጊ ግጭቶችን፣ ሞትን፣ የአካል ጉዳትንና መፈናቀልን ፈጠረ እንጂ የህዝብን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ሊያፍነዉ አልቻለም። የተቀሩትም ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ ያቀረብ ብሄሮች ጥያቄያቸዉ እንደ ጤዛ ተኖ ይጠፋል ማለት ከታሪክ መማር አለመቻል ነዉ። ኢትዮዽያ ብሄሮቿን በእኩልነት ማስተናገድ እስካቻለች ድረስ ሰላማዊት፣ ፍትሃዊትና ዴሞክራሲያዊት ልትሆን በፍጹም አትችልም።